የኑሮ ውድነት ለመቋቋም በአጭር ጊዜ የሚደርሱ የጓሮ አትክልቶችን እያለማን ነው – በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ሞዴል አርሶአደሮች
እያጋጠመው ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሰብሎች ወጪውን ከመቀንስ ያለፈ የገቢ ምንጭ እየሆነ መጥቷል አሉ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ሞዴል አርሶአደሮች ፡፡
የሞዴል አርሶአደሮችን ተሞክሮ በማስፋፋት ለገበያ የሚበቃ ምርት በማምረት የኑሮ ውድነትን ችግር ለማቃለል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
አቶ ፋንታሁን ተክለ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ የዳራሮ ቀበሌ ታታሪ አርሶአደር ናቸው፡፡መተዳደሪያቸው ግብርና ሥራ በመሆኑ የተለያዩ ምርት በማምረት ከምግብ ፈጆታ ያለፈው ምርቱን ለገበያ በማቅረብ በሚያገኙት ገቢ በኑሮአቸው መሻሻሎችን ማየታቸውንና ልጆቻቸውን በአግባቡ ለማስተማር ማብቃታቸውን ተናግረዋል፡፡
ከቋሚ ተክል ጀምሮ እስከ ጓሮ አትክልት በማምረት ወጪውን ከመቆጠብ ባለፈ ማር፣ ቡናና ቆጮ ለገበያ በማቅረብ በአመት ከፍተኛ ውጤት እያገኙ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
አርሶአደሩ ከባህላዊ ንብ ማነብ ሥራ ወደ ዘመናዊ ተሸጋግሯል፡፡ በዚህም ጠቀም ያለው ገቢ እያገኙ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
አቶ ፋንታሁን የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበረ ጠቅሰው በአከባቢው ሌሎች አርሶአደሮችን እንደ እርሱ ሞዴል ለማድረግ ተሞክሮአቸውን በማካፈል ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል
የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍለ ጅግሦ እንደ ሀገር የተጀመረው ምግቤን ከጓሮዬ ተግባርን በማጠናከር የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል
በተለይም የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ከሚሠሩ ሥራዎች መካከል በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ሰብሎች በስፋት እየተሠራ ነው ያሉት አቶ ክፍለ በዚህም ጽ/ቤቱ የግብዓት ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በኤክስቴንሽን ባለሙያ ተገቢ ድጋፍ በማድረግ ተሞክሮአቸውን ለማስፋፋት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ ፡ እምነት ሽፈራው- ከፍስሀ ገነት ጣቢያችን
More Stories
ያመረትናቸውን ምርቶች ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚነታችንን እያረጋገጥን ነው – በጌዴኦ ዞን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ማህበራት
የጂንካ መምህራን ማህበር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር የአባላት ጥቅም በማስጠበቅ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ሥርዓት እንዲሰፍን ጠንክሮ እንደሚሠራ አስታወቀ
በማህበራትና በዩንየን ተደራጅተዉ የሚሠሩ ቡና አልሚ አርሶ አደሮች በጥራት ማምረትና ማቅረብ ላይ ሁሌም ትኩረት ሊሰጡ ይገባል – የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ