በበጀት ዓመቱ ከ379 ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በበጀት ዓመቱ ከ379 ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉባኤው ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ ከ379 ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል።
በገጠርና በከተማ የስራ ፈላጊዎችን በመለየትና በመመዝገብ ወደ ተግባር መገባቱን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለ379 ሺ 430 ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን በሪፖርታቸው ጠቁመዋል።
በክልሉ ከ60 ሺ በላይ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፈጠሩንም የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ከእነዚህ ውስጥ 39 ሺ 879 ወደ ቋሚ እንዲሸጋገሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ኢንተርፕራይዞች ተኪ ምርት እንዲያመርቱ በተደረገው ትኩረት 210 ያህሉ 5354 ቶን በማምረት 19 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ማዳን ስለመቻሉም ገልፀዋል።
በበጀት አመቱ 637 ሚሊዮን 210 ሺህ 422 ብር ብድር መሰራጨቱን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለኢንተርፕራይዞች ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን በላይ ብር የገበያ ትስስር ተፈጥሯል ብለዋል።
ዘጋቢ፡ መለሰች ዘለቀ

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል