በበጀት አመቱ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በበጀት አመቱ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሔደ ነው።
በበጀት አመቱ ከማዘጋጃ ቤታዊና ከመደበኛ ገቢ 26 ቢሊዮን 607 ሚሊዮን 38 ሺህ ብር መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።
አፈፃፀሙም ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው ርዕሰ መስተዳደሩ በሪፖርታቸው ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ መለሰች ዘለቀ

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል