የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንና የንግድ ትርዒት ተከፈተ
የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንና የንግድ ትርዒት በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) እና በሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ ተከፍቷል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ የሀዲያ ብሔር ቱባ ባህላዊ እሴቶችን የሚገልጹ ቁሳቁሶች፣ የግብርና ውጤቶች፣ የቱሪስት መስህቦች፣ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተመረቱ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጎብኝቷል።
በኤግዚቢሽኑ ላይም በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አካባቢያቸውን የሚያሳዩ ምርቶችን ይዘው ቀርበዋል።
ዘጋቢ፡ ተሻለ ከበደ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በትምህርቱ ዘርፍ ላይ መስራት የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ መስራት እንደሆነ ተገለጸ
ኒው ዳውሮ ፋውንዴሽን ከ600 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ
በኮሬ ዞን የሣርማሌ ወረዳ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ የጋራ ውይይት አደረገ