በኮሬ ዞን የሣርማሌ ወረዳ የፀጥታ ምክር ቤት ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ የጋራ ውይይት አደረገ
የውስጥና የውጭ ፀጥታ መረጋጋት ለዘላቂ ሠላምና ልማት መሠረት መሆኑ ተመላክቷል።
በውይይቱ የሣርማሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኢዩኤል ጠንካራ የተሽከርካሪ የሰአት ገደብ ያለመኖር፣ የገበያ ትሥሥርና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ለፀጥታ ስጋት መንስኤ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
አክለውም አቶ ኢዩኤል የውስጥና የውጭ ፀጥታን በዘላቂነት ለማረጋጋት በቅንጅት መሥራት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።
የወረዳው ምክትል ኃላፊ አቶ ኢሳያስ ገብሬ የአካባቢውን ፀጥታ ለማስጠበቅ ትክክለኛ መረጃ መለዋወጥ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።
የሣርማሌ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጌታሁን የወረዳውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከቀድሞ በተሻለ ሁኔታ የሥጋት ቀጠናዎችን በመለየት ጠንክሮ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ተሳታፊዎችም ለወረዳው ዘላቂ ሠላምና ፀጥታ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽንና የንግድ ትርዒት ተከፈተ
በትምህርቱ ዘርፍ ላይ መስራት የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ መስራት እንደሆነ ተገለጸ
ኒው ዳውሮ ፋውንዴሽን ከ600 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ