ብራዚላዊው የመሐል ሜዳ ተጫዋች ብሩኖ ጊማሬስ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል የሚያደርገውን የ75 ሚሊዮን ፓውንድ ዝውውር ተከትሎ የሕክምና ምርመራውን በሙሉ ስኬታማ በሆነ መንገድ ማጠናቀቁ ተገልጿል።
ተጫዋቹ በኢሚሬትስ ለአራት ዓመታት የሚያቆየውን የኮንትራት ውል በይፋ የሚፈርም ሲሆን፥ መድፈኞቹም ዝውውሩን በይፋ ለማብሰር የመጨረሻ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ ይገኛሉ።
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ትናንት ጠዋት ከተጫዋቹ ጋር በስልክ ተገናኝቶ የተወያየ ሲሆን፥ በቡድኑ የጨዋታ ስልት ውስጥ የሚኖረውን ቁልፍ ሚና እና ስለሚሰጠው ኃላፊነት ማብራሪያ መስጠታቸው ተዘግቧል።
አርቴታ ብሩኖን የክለቡ የረጅም ጊዜ እቅድ አካል በማድረግ ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበረው ይታወቃል።
ብሩኖ ጊማሬስ በኒውካስል ቆይታው አሳይቶት የነበረው አስደናቂ ብቃት፣ የአመራርነት ክህሎት እና የጨዋታ ፍላጎት አርሰናልን በመሐል ሜዳ ላይ የበለጠ ጠንካራ እንደሚያደርገው ይታመናል።
ክለቡ የዝውውሩን ማጠናቀቂያ ቪዲዮ እና የፎቶ ፕሮግራም እያዘጋጀ ሲሆን፥ በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ዝውውሩ መጠናቀቁ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
ብሩኖ ጊማሬስ የሕክምና ምርመራውን በስኬት አጠናቀቀ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ