“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ፖል ሜርሰን ፕሪሚየር ሊጉን እየመራ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ አሁን ባለው የሜዳ ላይ አቋም ከቀጠለ የሊጉን ዋንጫ የማንሳት ዕድል “ፈጽሞ የለውም” ሲል አስተያየት ሰጥቷል።
ኤንዞ ማሬስካ የሚመራው ማንቸስተር ሲቲ በትናንትናው ዕለት ሰንደርላንድን 5 ለ 3 በመርታት የመጀመሪያዎቹን አምስት ሊግ ጨዋታዎች በድል በማጠናቀቅ ድንቅ ጅምር አድርጓል።
በዚህም ሻምፒዮኑ አርሰናል በብራይተን 3 ለ 0 መረታቱን ተከትሎ ሲቲዎች ከአርሰናል በሶስት ነጥብ ርቀት ሊጉን እየመሩ ለሶስት ሳምንታት ወደ ሚቆየው የዓለም አቀፍ የሀገር የጨዋታ ሰሞን ፊታቸውን አዙረዋል።
ሜርሰን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ማንቸስተር ሲቲ ሁል ጊዜ እንዲህ የሚጫወት ከሆነ ሊጉን ሊያሸንፍ የሚችልበት ምንም መንገድ የለም። ሁል ጊዜ ብዙ ግቦችን እያስቆጠሩ ብቻ ማሸነፍ አይቻልም፤ በዚህ ዓይነት አጨዋወት መቀጠል ከባድ ነው። ትልልቅ ቡድኖች እንዲህ ዓይነቱን ክፍተት ተጠቅመው ይቀጡሃል“ ብሏል።
ሰንደርላንድ በሀገሪቱ ብዙ ግቦችን ከሚያስቆጥሩ ክለቦች መካከል የማይመደብ መሆኑን የገለፀው ሜርሰን፤ ሆኖም በሲቲ ላይ ሶስት ግቦችን ማስቆጠር መቻሉን እና ከዚህም በላይ ማግባት እንደሚችሉ ጠቁሟል። የሲቲ የፊት መስመር ጥቃት ጥሩ ቢሆንም፣ የኋላ መስመራቸው ግን ፈጽሞ የተበታተነ መሆኑንና ይህ ድክመት በተለይ ከታላላቆቹ ክለቦች ጋር ሲጫወቱ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው አስገንዝቧል።
ሰንደርላንድ በፕሪሚዬር ሊጉ ብዙ ግቦችን ከሚያስቆጥሩ ክለቦች መካከል የማይመደብ መሆኑን የገለፀው ሜርሰን፤ ሆኖም በሲቲ ላይ ሶስት ግቦችን ማስቆጠር መቻሉን እና ከዚህም በላይ ማግባት ይችሉ እንደነበር ጠቁሟል።
የሲቲ የፊት መስመር ማጥቃት ጥሩ ቢሆንም፣ የኋላ መስመራቸው ግን ፈጽሞ ያልተደራጀ መሆኑንና ይህ ድክመት በተለይ ከታላላቆቹ ክለቦች ጋር ሲጫወቱ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው አስገንዝቧል።
ማንቸስተር ሲቲ ቀጣይ የሊግ መርሃ ግብሮቹን አሸናፊ ሆኖ ለመቀጠል የመከላከል ድክመቱን በአፋጣኝ ማስተካከል እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥቷል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን

More Stories
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ
ቶትንሃም በአስቶንቫላ ተሸነፈ