9 ክለቦች በአዲስ አሰልጣኞች ፍልሚያቸውን የሚጀምሩበት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ
የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ገና ሳይጀምር አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
በዚህ የውድድር ዘመን የመክፈቻ ሳምንት 9 ያህል ክለቦች በአዲስ አሰልጣኞች መሪነት ወደ ሜዳ የሚገቡ ሲሆን ይህም በሊጉ ታሪክ በመክፈቻ ሳምንት ከፍተኛው የአሰልጣኞች ለውጥ የተደረገበት ወቅት አድርጎታል።
የዚህ ታሪካዊ ለውጥ የቅርብ ጊዜው እና ትልቁ ማጠቃለያ የኒውካስል ዩናይትድ ውሳኔ ነው።
የሳውዲውን አል-አህሊ ክለብ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የኤሺያ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ያደረጉት ጀርመናዊው አሰልጣኝ ማትያስ ያይስለ፣ ኤዲ ሃውን በመተካት የሴንት ጄምስ ፓርኩን ክለብ በ4 ዓመት ኮንትራት ተረክበዋል።
ኒውካስል የ38 ዓመቱን ታክቲሺያን ለማስፈረም 9.5 ሚሊዮን ፓውንድ የካሳ ክፍያ ለሳውዲው ክለብ ፈፅሟል።
በዚህም ማግፓይሶቹ በአዲስ አሰልጣኝ አዲሱን የውድድር ዘመን የሚጀምሩ 9ኛው ክለብ ሆነዋል።
አጠቃላይአዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት 9 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ስንመለከት፥ ኒውካስልዩናይትድ፦ ማትያስ ያይስለ፣ ሊቨርፑል፦ አንዶኒ ኢራኦላ፣ማንቸስተር ሲቲ፦ ኤንዞ ማሬስካ፣ ቼልሲ፦ሻቪ አሎንሶን በአዲስ መልክ መቀጠራቸው ይታወቃል።
በተጨማሪም ቦርንመዝ፦ ማርኮ ሮዜ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት፦ ኦሊቨር ግላስነርን ክሪስታል ፓላስ፦ ፒየር ሳጅ፣ ፉልሃም፦ አልቫሮ አርቤሎአ እንዲሁም፣ አይፕስዊች ታውን፦ ጋሪ ኦኔል በአዲስ መልክ የቀጠሩ ሌሎች ክለቦች ናቸው።
ከዚህ ቀደም ከፍተኛው የመክፈቻ ሳምንት የአሰልጣኞች ለውጥ የተመዘገበው በ2016/17 የውድድር ዘመን ሲሆን 8 ክለቦች በአዲስ አሰልጣኝ ጀምረው ነበር።
የዘንድሮው የ9 ክለቦች ለውጥ ከ1946/47 በኋላ በከፍተኛው የእንግሊዝ ሊግ እርከን ታሪክ የመጀመሪያው ነው።
እ.ኤ.አ በታህሳስ 2019 የተቀጠሩት የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን በፕሪሚየር ሊጉ ረጅም ጊዜ የቆዩ አሰልጣኝ ሆነዋል።
በመክፈቻው ሳምንት ፉልሃም ከ ቼልሲ፣ ማንቸስተር ሲቲ ከ ቦርንመዝ እንዲሁም ኒውካስል ከ ሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታዎች በሁለቱም በኩል በአዲስ አሰልጣኞች የሚመሩ በመሆናቸው የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ብሩኖ ጊማሬስ የሕክምና ምርመራውን በስኬት አጠናቀቀ
ሁለተኛው ዙር የሲዳማ ቡና አትሌክስ ክለብ የታዳጊዎች ምልመላ ውድድር እየተካሄደ ነው
ሞሐመድ ሳላህ ወደ ቱርኩ ትራብዞን ስፖር የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ኢስታንቡል ገብቷል