ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ

ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ

ከ1 ሺህ 500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተጀምሯል።

ውድድሩን ከፍተኛ የክልል አመራሮች እንዲሁም ሀገራችንን በተለያዩ የሩጫ መድረኮች ያስጠሩት አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም፣ አትሌት ሙክታር እድሪስ እና አትሌት አየለ አብሽሮን ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አስጀምረዋል።

ዘጋቢ፡ ዳዊት ዳበራ – ከወልቂጤ ጣቢያችን