ሁለተኛው ዙር የሲዳማ ቡና አትሌክስ ክለብ የታዳጊዎች ምልመላ ውድድር እየተካሄደ ነው
በምዘና ውድድሩ ላይ ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 18 የሆናቸው ከክልሉ 12 ወረዳዎች የተውጣጡ ከ300 በላይ ታዳጊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ብዙነህ ታቦታ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ክልሉ ለአትሌቲክስ ስፖርት አቅም ካላቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ መሆኑን በመጠቆም የሲዳማ ቡና አትሌቲክስ ክለብም ታዳጊዎች ላይ የጀመራቸው ስራዎች ከወዲሁ አመርቂ ውጤት እንደተገኘበት ገልፀዋል።
ሀላፊው አክለውም የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን በክልሉ ለአትሌቲክስ ስፖርት አቅም ያላቸውን አካባቢዎችን በመለየት የማዘውተሪያ ስፍራዎች የማልማት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሲዳማ ቡና አትሌቲክስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ደበሳ፤ ክለባቸው ታዳጊዎች ላይ እያከናወናቸው ያለው ስራዎች ለሌሎች አትሌቲክስ ክለባት ሞሳሌ እንደሚሆን በመግለፅ እንደ ሀገር ችግር የሆነውን የዕድሜ ተገቢነት ጥያቄ ለመቅረፍ በተደራጀ መልኩ ስራዎች እንደተከናወኑ ጠቁመዋል።
በ2017 በተካሄደው አንደኛው የምዘና ውድድር 24 አትሌቶች ወደ ተለያዩ አትሌቲክስ ክለባት የገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 21 አትሌቶች ሲዳማ ቡና አትሌቲክስ ክለብን ተቀላቅለዋል።
ውድድሩ ነገ ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን በዕለቱ በርካታ የፍፃሜ ውድድሮች ይከናወናሉ።
ዘጋቢ፡ ግዛቸው ደሳለኝ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ