የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የከምባታ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ
በመላው ሀገሪቱ “በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሀግብር በከምባታ ዞን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ሄራሞ አስታውቀዋል፡፡
በነገው ዕለት ችግኝ ተከላ የሚደረግበትን ስፍራ ምልከታ ያደረጉት አቶ ተሾሙ፤ ለመርሀ ግብሩም ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው 1.6 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።
ከ486 ሄክታር በላይ መሬት ተለይቶ የጉድጓድ ዝግጅት እና በተመረጡ 44 የተከላ ቦታዎች የችግኝ አቅርቦት መጠናቀቁን ያነሱ ሲሆን በተከላውም ከ185 ሺህ በላይ ህዝብ እንደሚሳተፍ ገልጸዋል።
አቶ ተሾመ አያይዘውም፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት እንደ ሀገር በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው በያዝነው ዓመትም በዋናነት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸውና የምግብ ዋስትና ሊያረጋግጡ በሚችሉ የፍራፍሬ ችግኞች እና የቡና ችግኞች በዞኑ እየተተከሉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም አቶ ተሾመ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ህፃናት፣ አዋቂዎች፣ በሁሉም የሙያ መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች ጨምሮ መላው የከምባታ ህዝብ ከማለዳው 12:00 ጀምሮ በመውጣት አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ ምስጋና ኤልያስ

More Stories
በጎፋ ዞን በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ8 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ
ነገ በአንድ ቀን ጀምበር 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ
በቀቤና ልዩ ወረዳ ለአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የልዩ ወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ