በጎፋ ዞን በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ8 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ
የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደግፌ፤ ነገ በሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ8 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር መርሃ ግብር እንደሚተከሉ ተናግረዋል።
3 ሺህ 382 ነጥብ 9 ሄክታር የተከላ ቦታ መዘጋጀቱን ያብራሩት ኃላፊው፤ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችና ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች እንደሚተከሉ አንስተዋል።
148 በጂኦ ሎኬሽን የተመዘገቡ የተከላ ቦታዎች እንዲሁም 4,148,375 በጂኦ ሎኬሽን ቦታዎች የሚተከሉ ችግኞች መዘጋጀታቸውን አስረድተዋል።
በዞኑ ከ81 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በደን ስለመሸፈኑ ያብራሩት ኃላፊው የደን ሽፋኑ ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 21 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት በተከናወነ የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር የዞኑ አየር ጸባይ እየተስተካከለ መምጣቱንና የደረቁ ምንጮች መፍለቅ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
የተተከሉ ችግኞች የመልክአ ምድሩን ገጽታ መቀየር የቻሉ እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ያላቸው አበርክቶ የላቀ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
መላዉ የዞኑ ነዋሪዎችም ለተከላው በነቂስ ወጥተው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የከምባታ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ
ነገ በአንድ ቀን ጀምበር 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ
በቀቤና ልዩ ወረዳ ለአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የልዩ ወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ