አርሰናል የብሩኖ ጊማራኤስን ዝውውር ለማጠናቀቅ ከስምምነት ደረሰ!
አርሰናል የኒውካስል ዩናይትድ እና የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ብሩኖ ጊማራኤስን በይፋ ለማስፈረም የሚያስችለውን የ80 ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት መፈጸሙን ዘ ሳንዴይ ታይምስ ዘግቧል።
የ28 ዓመቱ ብሩኖ ጊማራኤስ፣ በነገው ዕለት በለንደን ተገኝቶ የህክምና ምርመራ እንደሚያደርግ እና የአምስት ዓመት ኮንትራት እንደሚፈርም ተጠቅሷል።
ሚኬል አርቴታ የመሃል ሜዳ ክፍላቸውን የበለጠ ለማጠናከር እና በቀጣዩ የውድድር ዘመን ውስጥ ሊጎች እና በአውሮፓ መድረክ በጠንካራ ሁኔታ ለመፎካከር ብሩኖ ጊማራኤስን ቀዳሚ ኢላማቸው አድርገውት ቆይተዋል።
ጊማራኤስ ኳስ የመንጠቅ፣ ጨዋታ የመምራት እና ጥቃቶችን የመመስረት ከፍተኛ ብቃት ያለው በመሆኑ ለአርሰናል የመሃል ክፍል ትልቅ ተጨማሪ ኃይል ይሆናል ተብሎ ይገመታል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ