ሪያል ማድሪድ ሮድሪ ለማስፈረም ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ አቀረበ!
የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የማንቼስተር ሲቲውን አማካይ ሮድሪን ወደ ሳንቲያጎ በርናቤው ለማስኮብለል የመጀመሪያውን ይፋዊ እርምጃ ወስዷል።
በሁለቱ የአውሮፓ ሀያላን ክለቦች መካከል የመጀመሪያ ደረጃ የቃል ድርድር በይፋ መጀመሩን ፋብሪዚዮ ሮማኖ ዘግቧል።
የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ለወራት ተዘጋግቶ የነበረውን በር በመክፈት ዝውውሩ እንዲገፋበት ሙሉ ፈቃዳቸውን ሰጥተዋል።
ሎስ ብላንኮሶቹ ለ30 ዓመቱ አማካይ ዝውውር ከ50 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ለማውጣት ዝግጁ መሆናቸውን ለሲቲ ባለስልጣናት አሳውቀዋል።
ድርደሩ በአሁኑ ወቅት በቃል ደረጃ ያለ ቢሆንም፤ የሪያል ማድሪድ ፍላጎት ወደ ተግባር መሸጋገሩን ያሳያል።
ሪያል ማድሪድ ለአማካይ ክፍሉ ተጨማሪ ጥንካሬ እና መረጋጋት ለመስጠት ሮድሪን ቀዳሚ ኢላማው አድርጎታል።
ተጫዋቹ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ያለው ኮንትራት ወደ መጨረሻው ዓመት እየተቀረበ በመሆኑ እና እስካሁን የውል ማራዘሚያ ባለመፈረሙ ሪያል ማድሪድ ይህንን አጋጣሚ ለመጠቀም እንቅስቃሴ ጀምሯል።
የዓለም ዋንጫ ወርቅ ኳስ አሸናፊው ሮድሪ ወደ ሀገሩ ስፔን የመመለስ ፍላጎት እንዳለው የሚገለጽ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት በሁለቱ ክለቦች መካከል የሚደረገው ንግግር ወደ ጠንካራ የገንዘብ ጥያቄ ይሸጋገራል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቼስተር ዩናይትድ በዝውውር ገበያው አዳዲስ አማራጮችን እየተመለከተ ነው
ሮቤርቶ ማንቺኒ ወደ ጣሊያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ሊመለሱ እንደሆነ ተገለጸ
ዚነዲን ዚዳን የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ