የአባቱ ልጅ!
የቀድሞው የባርሴሎና እና የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሮናልድ ኩማን በተከላካይ ስፍራ እየተጫወተ በማይታመን የግብ ማስቆጠር ብቃቱ እና በፍፁም ቅጣት ምት ኤክስፐርትነቱ በዓለም እግር ኳስ ስሙ በወርቅ የተጻፈ ታሪካዊ የእግርኳስ ሰው ነው።
አሁን ደግሞ ልጁ ሮናልድ ኩማን ጁኒየር የአባቱን እግር ተከተሎ በደች እግር ኳስ አዲስ ታሪክ ሰርቷል—ነገር ግን ለየት በሚል መልኩ፣ እሱ ግብ ጠባቂ ነው!
በኤረዲቪዚ የ31 ዓመቱ የቴልስታር ግብ ጠባቂ ኩማን ጁኒየር ቡድኑ ከካምቡር ጋር ባደረገው ጨዋታ በ2-2 አቻ ውጤት እንዲለያይ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶችን ማስቆጠር ችሏል።
ቡድኑ 2 ለ 0 እየተመራ እና በአንድ ተጫዋች ጎድሎ በነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታ፣ ኩማን ጁኒየር በ63ኛው ደቂቃ የመጀመሪያውን ጎል ሲያስቆጥር፣ ሁለተኛዋን ደግሞ ጨዋታው ተጠናቆ በተጨመረው 11ኛ ደቂቃ (በ101ኛ ደቂቃ) መረብ ላይ በማሳረፍ ቡድኑን ከሽንፈት ታድጓል።
ይህም በኔዘርላንድስ ከፍተኛ ሊግ ታሪክ በአንድ ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው ግብ ጠባቂ ያደርገዋል።
ኩማን ጁኒየር ይህን ያደረገው ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።
ባለፈው ግንቦት ወር ቡድኑ ከቮለንዳም ጋር ባደረገው ወሳኝ ጨዋታ በ88ኛው ደቂቃ ፍፁም ቅጣት ምት በማስቆጠር ቴልስታር ከወራጅ ቀጠናው ዞን እንዲያመልጥ አድርጎ ነበር።
አባቱ ሮናልድ ኩማን በተጫዋችነት ዘመኑ 239 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 115 ያህሉ በፍፁም ቅጣት ምት የተገኙ ነበሩ።
ኩማን ጁኒየር ይህንን የወረሰውን ከፍፁም ቅጣት ምት የማስቆጠር ጥበብ አሁን በግብ ጠባቂነት ቦታ ላይ ሆኖ እያሳየ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
የአባቱ ልጅ!

More Stories
ቼልሲ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን አስፈረመ
ማንቼስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ድሉን ፍለጋ ከኢፕስዊች ጋር ይፋጠጣል
ሚካኤል አርቴታ ለአርሰናል 250ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ሊመሩ ነው