ቼልሲ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን አስፈረመ
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የአስቶንቪላውን እና የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የግብ መስመር ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን በ7.5 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።
እድሜው 33 የደረሰው የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ግብ ጠባቂ በስታምፎርድ ብሪጅ ለሶስት ዓመታት የሚቆይ ኮንትራት ተፈራርሟል።
ማርቲኔዝ ቼልሲ ማመራቱን ተከተሎ በሰጠው አስተያየት “በዚህ ታላቅ ክለብ በመገኘቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ። ወደ ቼልሲ መምጣት ለኔም ሆነ ለቤተሰቤ በጣም ቀላል ውሳኔ ነበር፤ በመምጣቴም በጣም ተደስቻለሁ፣ ስራዬን ለመጀመርና ወደ ሜዳ ለመግባት ጎጉቻለሁ” ብሏል።
ግብ ጠባቂው አክሎም “እዚህ ስኬታማ መሆን እፈልጋለሁ፤ እኔ በምሳተፍበት ነገር ሁሉ ማሸነፍ የምፈልግ ሰው ነኝ” ሲል ፍላጎቱን ገልጿል።
የማርቲኔዝ ወደ ቼልሲ መምጣት የክለቡን የግብ መስመር ልምድ ባላቸው እና ዋንጫ መሸነፉ ተጫዋቾች ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቼስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ድሉን ፍለጋ ከኢፕስዊች ጋር ይፋጠጣል
ሚካኤል አርቴታ ለአርሰናል 250ኛ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ሊመሩ ነው
የሊቨርፑል እና ኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ