ሮቤርቶ ማንቺኒ ወደ ጣሊያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ሊመለሱ እንደሆነ ተገለጸ
የቀድሞው የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ እንደገና የአዙሪዎቹ (የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን) ዋና አሰልጣኝ ሆነው ለመሾም ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተዘግቧል።
ቀደም ሲል የቀድሞው የቡድኑ ኮከብ እንድሪያ ፒርሎ አዲሱ የጣሊያን አሰልጣኝ ሆኖ ለመሾም ስምምነት ላይ ተደርሶና የፊርማ ስነ-ስርዓት ብቻ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ጆቫኒ ማላጎ በድንገት ድርድሩን አቋርጠውታል።
ለዚህም በምክንያትነት የቀረበው ፒርሎ ከሩሲያ ኩባንያ ጋር ያለው የንግድ ትስስር እና ትብብር መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎም የፒርሎን ወደ አዙሪዎቹ አሰልጣኝነት መምጣት አጠናክረው ሲሰሩ የነበሩት የጣሊያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሮጀክት አመራሮች ማለትም ታላቁ ፓኦሎ ማልዲኒ እና ሊዮናርዶ ከፌዴሬሽኑ ኃላፊነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸው ታውቋል።
በዚህ ያልተጠበቀ እጣ ፈንታ ምክንያት ፌዴሬሽኑ ፊቱን ወደ ቀድሞው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ያዞረ ሲሆን ማንቺኒም በቅርብ ቀናት ውስጥ የኮንትራት ውላቸውን ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ማንቺኒ ከዚህ ቀደም ጣሊያንን የዩሮ 2020 ዋንጫ አሸናፊ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቼስተር ዩናይትድ በዝውውር ገበያው አዳዲስ አማራጮችን እየተመለከተ ነው
ዚነዲን ዚዳን የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
ሪዮ ፈርዲናንድ ዳኒ ዌልቤክ ቼልሲን ትቶ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እንዲመለስ ጥሪ አቀረበ