የኦዲት አገልግሎት ቅልጥፍናና ጥራት በማሣደግ የተገልጋይና የባለድርሻ አካላት ርካታን ለማሣደግ እየተከናወነ በሚገኘው ተግባር ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን የክልሉ ዋና ኦዲተር አስታወቀ

የኦዲት አገልግሎት ቅልጥፍናና ጥራት በማሣደግ የተገልጋይና የባለድርሻ አካላት ርካታን ለማሣደግ እየተከናወነ በሚገኘው ተግባር ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን የክልሉ ዋና ኦዲተር አስታወቀ

በተያዘው የበጀት ዓመት ኦዲት ተደራጊ መስሪያ ቤቶች በመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን መሠረት በማድረግ ዕቅዶቻቸውን በቁጠባና በቅልጥፍና እንዲያከናወኑ በሥልጠና እንደሚያግዝ ተገልጿል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ለ6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 10 መደበኛ የምክር ቤት ጉባኤ ቀርቧል።

የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ አስራት አበበ፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የመንግሥት ፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት፣ የክዋኔና አካባቢ ኦዲት፣ ልዩ ኦዲት፣ የገቢ አዲት፣ ንብረት ኦዲት፣ የክልል የተጠቃለለ ገቢና ወጪ ኦዲት በድምሩ 45 ኦዲቶች ማከናወናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ኦዲት በሽፋን 47 ከመቶ ሲሆን ከእቅድ አፈጻጸም አንጻር ከ86.6 እጅ በላይ መሆኑም ተጠቁሟል።

በተከናወነው ተግባር የተገልጋይና የባለድርሻ አካላት ርካታን 84.4 በመቶ ለማድረስ መቻሉንም በሪፖርታቸው አብራርተዋል።

አሁን ላይ የኦዲት ግኝት አመላለስ ላይ በተከናወነው የተቀናጀ ርብርብ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱም ተገልጿል።

በክልሉ የሚገኘውን ሃብት በአግባብና በሥርዓት እንዲመራ ለማስቻል የተጠናከረ ሥራ እየተሠራ ይገኛልም ተብሏል።

በክልሉ አሁን ላይ ከነቀፌታ ነጻ የሆኑ ተቋማትንም ለመፍጠር እየተከናወነ የሚገኘውን ተግባር በማገዝ በኩል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ተጠይቋል።

በ2019 በጀት ዓመት ከ42 መስሪያ ቤቶች በላይ ኦዲት ለማድረግ መታቀዱንና ሽፋኑንም ወደ 64 በመቶ ለማድረስም እንደሚሠራም አቶ አሥራት ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከቦንጋ ማስተባበሪያ