በክልሉ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ፋና ወጊ ለውጥ ለማስመዝገብ በመሰራቱ አበረታች ለውጦች ተመዝግበዋል – አቶ ጥላሁን ከበደ
ሀዋሳ፡ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ፋና ወጊ ለውጥ ለማስመዝገብ በመሰራቱ አበረታች ለውጦች ተመዝግበዋል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡
ጳጉሜን 5 “የነገው ቀን” የኢትዮጵያ ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል በአርባምንጭ ከተማ ተከብሯል።
የደቡብ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ቦጋለ ቦሼ (ዶ/ር)፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ሆና በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚያዊ እና በሌሎች ዘርፎች በዲጂታል የታገዘ ማንሰራራት ማሳየቷን ተናግረው ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጋ በመስራቷ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን አስመዝግባለች ብለዋል።
በቱሪዝም ዘርፍ በሀገራችን ብሎም በክልላችን የሚታይ ለውጥ መመዝገቡን ያብራሩት ዶ/ር ቦጋለ፤ ዘርፉ የአግሮ ኢንዱስትሪው ላይ እመርታዊ ለውጥ እንዲመዘገብም አወንታዊ ሚና ተጫውቷል ሲሉ ተናግረዋል።
በማዕድን ዘርፍም በ2018 በጀት ዓመት አበረታች ስኬት መመዝገቡን እና ይህም ለውጥ በዲጂታል ቴክኖሎጂ መታጀቡን ጠቁመው፤ ዓመቱ ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ ሆኖ የተጠናቀቀበት ዓመት በመሆኑም ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ገልጸዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው፤ ሀገራችን በ2018 ዓ.ም በውስብስብ ችግሮች ውስጥ ሆና በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው እና ማህበራዊ ዘርፍ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል።
”የነገ ቀን” ዛሬ ስናከብር የዲጂታል ዓለም ላይ ፋና ወጊ ለውጥ ማስመዝገብ ይጠበቅብናል ያሉት አቶ ጥላሁን፤ ውስብስብና አሰልቺ አሰራሮችን የመፍታት ታሪካዊ ሀላፊነት እንደአለብንና በዲጂታል የታገዘ የምርት እድገት በማስመዝገብ ብልፅግናችንን እውን ማድረግ ይጠበቅብናን ሲሉ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞዋን እውን ከማድረግ ባሻገር የበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ መሆኗን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ”የነገ ቀን” ስናከብር በቴክኖሎጂ ያደገና የተመነደገ ሀገር ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በፅናት መደገፍ ይጠበቅብናል።
በመጨረሻም አዲሱ አመት ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና ለክልሉ ህዝብ የሰላም፣ የጤና፣ የአብሮነትና የብልጽግና ዓመት እንዲሆን አቶ ጥላሁን ከበደ ተመኝተዋል።
በመርሀ ግብሩ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን፣ የከተማ እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
የተሳፋሪዎችን ደህንነትና ምቾት ለማስጠበቅ የትራንስፖርትና የትራፊክ ፖሊስ አካላት ቁጥጥራቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ተገለጸ
በካርበን ግብይት እና ሥነ-ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ላይ ትኩረት ያደረገ ሥልጠና ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለድርሻ አካላት ተሰጠ