ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
በዲጂታላይዜሽን ጉዞ የተከናወኑ የ“መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የ“5 ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ” ስልጠና እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ የነገን ከፍታ የሚወስኑ ሥራዎች በመሆናቸው እነዚህን በማሰብ “የነገው ቀን” መከበሩ የተለየ እንደሚያደርገው ተገልጿል።
የዕለቱን መርሐ ግብር በንግግር የከፈቱት የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ወገኔ ጌታቸው በመልዕክታቸው እንዳሉት፣ ዘንድሮ በዓመቱ መጨረሻ የነገውን ቀን ስናከብር ከወረቀት ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሪፎርም የምናደርገውን ጉዞ እውን ለማድረግ መትጋት እንዳለብን በማሰብ ነው ብለዋል።
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተረፈ ተካራ በበኩላቸው በእያንዳንዱ የጳጉሜን ቀናት የሚተላለፉ መልዕክቶች ለነገው ጉዞአችን ማቀድና መተግበር እንድንችል መነሻ ይሆናሉ ሲሉ አስረድተዋል።
ኢንጂነር ዮሐንስ ሀይሉ እና ወጣት አንተነህ ተኳሽ የተባሉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት፣ የትኞቹም ተግባራት ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እያደጉ በመሆናቸው ከአመራር ጀምሮ ሁሉም አካላት ክህሎትን ለማሳደግ መረባረብ አለባቸው ብለዋል።
ነገአችን እንዲሳካ ሲቪል ሰርቫንቱ 80 በመቶ ዲጂታል ተጠቃሚ እንዲሆንና በቀጣይም 12 በመቶ ለማሳደግ የተያዘውን ዕቅድ እውን ለማድረግ ከጊዜው ጋር መሄድ እንደሚጠበቅ በውይይቱ ተነስቷል።
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

More Stories
በክልሉ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ፋና ወጊ ለውጥ ለማስመዝገብ በመሰራቱ አበረታች ለውጦች ተመዝግበዋል – አቶ ጥላሁን ከበደ
የተሳፋሪዎችን ደህንነትና ምቾት ለማስጠበቅ የትራንስፖርትና የትራፊክ ፖሊስ አካላት ቁጥጥራቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ተገለጸ
በካርበን ግብይት እና ሥነ-ምህዳር አገልግሎት ክፍያ ላይ ትኩረት ያደረገ ሥልጠና ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለድርሻ አካላት ተሰጠ