በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ንግድን ለማስፋፋት የግሉ ዘርፍ የመሪነቱን ሚና ሊወስድ ይገባል -የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ንግድን ለማስፋፋት የግሉ ዘርፍ የመሪነቱን ሚና ሊወስድ እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።
የግሉ ዘርፍ የሚሳተፍበት በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ንግድ ያለበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ምክክር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በኢትዮጵያ ኢ-ኮሜርስ እንዲስፋፋ መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ መሆኑን ጠቁመው የግሉ ዘርፍ የመሪነቱን ሚና ሊወስድ ይገባል ብለዋል።
የኢ-ትራንዛክሽን አዋጅ፣ የግል ዴታ ጥበቃ፣ የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂ፣ የዲጂታል መታወቂያ እና የዲጂታል ክፍያ ስርአቶች ማስፋፋት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የኢኮሜርስ መስፋፋት የሚያግዙ የሙከራ ፕሮጀክቶች፣ ለጀማሪ የኢኮሜርስ ካሞፓኒዎች የፋይናንስ ድጋፎች እና ስልጠና፣ ኢኮሜርስን የሚመለከቱ የግንዛቤ ማሥስፋፊያ ፕሮግራሞች ተነድፈው ስራ ላይ እንዲውሉ መደረጉን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ የግሉ ዘርፍ እነዚህን ምቹ አጋጣሚዎች በመጠቀም ኢኮሜርስ ወደ ሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ እንዲሰሩም ጠይቀዋል።
ኢኮሜርስ የሚመራበት ሀገራዊ ስትራቴጂ ዝግጅት በሂደት ላይ መሆኑም ተጠቁሟል።
የኤሌክትሮኒክ ንግድ የሚመራበት የዕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በተለይም የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ፣ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ እና የዲጂታል ክፍያዎች እንደመደበኛ ክፍያ እንዲቆጠሩ ማድረግ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ውስጥ የተካተተ ነው።
ምንጭ ፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
More Stories
በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ ልማቶችን በጥናትና ምርምር አስደግፎ በመሥራት ረገድ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ
የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን በማስፋፋት የእርባታ ስራውን ምርታማነት የማሳደግና የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አፈር አልባ የመኖ አመራረት ዘዴን አስተዋወቀ