ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለጤና፣ ለግብርና እንዲሁም ለሃይል አቅርቦት ዘርፎች መጠቀም እንደምትፈልግ የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶር) ተናገሩ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለጤና፣ ለግብርና እንዲሁም ለሃይል አቅርቦት ዘርፎች መጠቀም እንደምትፈልግ የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶር) ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ከሩሲያው የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ አሌክሴይ ሌካቼቭ ጋር በኢትዮጵያ ለሚተገበረው የኒውክሌር ልማት ፍኖተ ካርታ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በርዱስ ፒተርስበርግ ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን የተፈረመው የአሁኑ የአፈጻጸም ሰነድ ከዚህ ቀደም የተፈረመውን ስምምነት ወደ ተግባር ለማስገባትና በዘርፉ ግልፅ አሰራርን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
የሩሲያው የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ አሌክሴይ ሌካቼቭ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት፤ በአቶሚክ ሳይንስ ላይ የኢትዮያውያን ባለሙያዎችን አቅም መገንባት የስምምነቱ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑን አንስተዋል።
ተቋሙ በ8 ሃገራት 33 የኒውክሌር ምርምር ማዕከላት ግንባታ ላይ እየሰሩ እንደሆነ አንስተዋል።
ዛሬ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ለስምምነት የበቃው የኒውክሌር ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፍኖተ ካርታ ኢትዮጵያ በዘርፉ የህክምና፣ የግብርና፣ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በምርምር ላይ ያላትን አቅም ለማዘመን ያስችላታል።
More Stories
አሰልጣኞች ወቅቱ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲላበሱ እየተሠራ መሆኑ ተጠቆመ
በቴክኖሎጂ የተካኑ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት በመሥራት ሀገሪቱን ማበልጸግ እንደሚገባ ተገለጸ
በቴክኖሎጂና ፈጠራ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት የኢንዱስትሪ ሽግግርን በማፋጠን የሃገር ኢኮኖሚ እንዲያድግ እየሰራ መሆኑን በስልጤ ዞን የቂልጦ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ገለፀ