አርሰናል ቪኒሺዬስ ጁኒየርን ለማስፈረም ሁኔታዎችን እየተከታተለ ነው
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሰናል የማጥቃት መስመሩን በከፍተኛ ደረጃ ለማጠናከር የሪያል ማድሪዱን የክንፍ ተጫዋች ቪኒሲየስ ጁኒየርን ለማስፈረም የሚችልበትን መንገድ እየቃኘ መሆኑ ተገልጿል።
የ 26 ዓመቱ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ኮከብ፣ መድፈኞቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ከያዟቸው በርካታ እጩዎች መካከል በግንባር ቀደምነት ከተቀመጡት ተጫዋቾች አንዱ መሆኑን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
አርሰናል ተጫዋቹን ለማስፈረም እንቅስቃሴ የሚያደርገው ቪኒሺዬስ በስፔን መዲና ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለውን ውል የማያራዝም ከሆነ ብቻ እንደሆነ ታውቋል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ያሳየው ፍላጎት ገና በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ሂደቱ በእርግጥ ወደ ተጨባጭ ዝውውር ስለመቀየሩ እስካሁን ምንም አይነት ዋስትና የለም።
አርሰናል በግራ ክንፍ የማጥቃት መስመሩ ላይ ተጨማሪ ጥራትና ፍጥነት ለመጨመር አማራጮችን እያየ ይገኛል።
ቪኒሺዬስ ጁኒዬር በሪያል ማድሪድ ቤት ያለው ውል ሊጠናቀቅ አንድ ዓመት እንደቀረው ይታወቃል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
በ22 ዓመቱ 7ኛ ክለቡን የተቀላቀለው ጆን ዱራን
ሮድሪ የፊታችን ሰኞ ቀዶ ጥገና ያደርጋል
ፔፕ ጓርዲዮላ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ጥሪን ውድቅ አደረጉ