ሮድሪ የፊታችን ሰኞ ቀዶ ጥገና ያደርጋል
የ2026 ዓለም ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሮድሪ የፊታችን ሰኞ የጀርባ ቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚያደርግ ክለቡ ማንቸስተር ሲቲ አሳውቋል።
ከስፔን ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማሸነፍ የቻለው ሮድሪ በህክምናው ምክንያት ለሁለት ወራት ያኽል ከሜዳ እንደሚርቅ ዘገባዎች አመላክተዋል።
የ30 ዓመቱ ሮድሪ ባለፈው ዕሁድ በተጠናቀቀው 23ኛው የዓለም ዋንጫ ወቅት ለላሮጃዎቹ በሁሉም ስምንት ጨዋታዎች ተሰልፎ በመጫወት ጥሩ አቋሙን አሳይቷል።
በማንቸስተር ሲቲ ቤት የአንድ ዓመት ኮንትራት የሚቀረው ሮድሪ በሲትዝኖቹ ቤት ያለው ቆይታ አልተረጋገጠም።
ሮድሪ ለሪያል ማድሪድ የመጫወት ፍላጎት እንዳለው መግለፁ ይታወሳል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ
ሮድሪ የፊታችን ሰኞ ቀዶ ጥገና ያደርጋል

More Stories
“እናቴ ሆይ ደውይልኝ!”
የአባቱ ልጅ!
ቼልሲ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን አስፈረመ