ዊሊያም ሳሊባ በጉዳት ምክንያት ለረዥም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል
ፈረንሳዊው የመሐል ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ ከባድ የጀርባ ጉዳት ማስተናገዱ ተረጋግጧል።
የአርሰናሉ ተከላካይ በዚህ ህመም ምክንያት ለረዥም ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።
የ25 ዓመቱ ዊሊያም ሳሊባ በ2026 ዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ፈረንሳይ በስፔን በተረታችበት ጨዋታ በ30ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል።
ሳሊባ ለወራቶች የቆየ የጀርባ ህመም እንደነበረበት የተነገረ ቢሆንም የወገብ ቀዶ ጥገና እንደማያደርግ ክለቡ አሳውቋል።
ተጫዋቹ ቀዶ ጥገና ባይደርግለትም በቂ የማገገሚያ ጊዜ በማስፈለጉ ቀኑ በግልጽ ባይታወቅም ለረዥም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ መድፈኞቹ አሳውቀዋል።
የዊሊያም ሳሊባን መጎዳት ተከትሎ ጆን ስቶንስ በአርሰናል ራዳር ውስጥ ገብቷል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ዶናልድ ትራምፕ ጂያኒ ኢንፋንቲኖን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ማድረግ ይፈልጋሉ
ጣሊያን ፔፕ ጓርዲዮላን ዋና አሰልጣኝ አድርጋ ለመሾም ንግግር ማድረግ ጀመረች
አርሰናል ብሩኖ ጊማሬሽን ለማስፈረም ከኒውካስል ጋር ቀጥታ ድርድር ጀምሯል!