አርሰናል ብሩኖ ጊማሬሽን ለማስፈረም ከኒውካስል ጋር ቀጥታ ድርድር ጀምሯል!
የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል የኒውካስል ዩናይትድ እና የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ቁልፍ አማካይ የሆነውን ብሩኖ ጊማሬሽን ወደ ኤሚሬትስ ለማምጣት እንቅስቃሴውን አፋጥኗል።
አርሰናል ደላሎችን በተጫዋቹ የዝውውር ጉዳይ ከኒውካስል የቦርድ አባላት ጋር ድርድር መጀመሩን ዘ ታይምስ ዘግቧል።
አርሰናል ዝውውሩን ለማፋጠን ሲል መደበኛ ባልሆኑ መንገዶች ጊዜ ከማባከን ይልቅ ከኒውካስል ጋር ፊት ለፊት መነጋገርን መርጧል።
የ28 ዓመቱ ብራዚላዊ አማካይ ወደ አርሰናል የመዛወር ፍላጎት እንዳለው እና ክለቡ እንዲለቀው ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።
አርሰናል እስከ £65 ሚሊዮን የሚደርስ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ኒውካስል ለተጫዋቹ ከ70 እስከ 80 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንደሚፈልግ ይነገራል።
መድፈኞቹ የአማካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር እና የዋንጫ ተፎካካሪነታቸውን ለማስቀጠል ጊማሬሽን ቀዳሚ ኢላማቸው አድርገውታል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ጣሊያን ፔፕ ጓርዲዮላን ዋና አሰልጣኝ አድርጋ ለመሾም ንግግር ማድረግ ጀመረች
ፊል ፎደን በማንቸስተር ሲቲ ቤት ውሉን አራዘመ
ቼልሲ ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈረመ