ፊል ፎደን በማንቸስተር ሲቲ ቤት ውሉን አራዘመ
ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ስድስት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫዎችን ያሸነፈው ፊል ፎደን በክለቡ ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።
ፊል ፎደን በማንቸስተር ሲቲ ቤት እስከ 2030 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ የአራት ዓመታት ውል መፈረሙን ክለቡ አሳውቋል።
የ26 ዓመቱ ፊል ፎደን ነባሩ ውል በቀጣይ ዓመት ይጠናቀቅ የነበረ ቢሆንም ውሉን ማራዘሙን ተከትሎ በልጅነት ክለቡ ለ20 ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።
በ17 ዓመቱ ለዋናው ቡድን ተሰልፎ መጫወት የጀመረው ፎደን እስካሁን 369 ጨዋታዎችን ለሲቲ አከናውኗል።
በነዚህ ጨዋታዎችም ከዜጋዎቹ ጋር 6 የፕሪሚዬር ሊግ፣አንድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ሁለት የኤፍኤ ካፕ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
አርሰናል ብሩኖ ጊማሬሽን ለማስፈረም ከኒውካስል ጋር ቀጥታ ድርድር ጀምሯል!
ቼልሲ ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈረመ
ትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሊ አህመድ አዲስ አበባ ገባ