ቼልሲ ሞርጋን ሮጀርስን በ117 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈረመ
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ሞርጋን ሮጀርስን የብሪታኒያ ክብረወሰን በሆነ የዝውውር ሒሳብ ከአስቶንቪላ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።
በአርሰናል በጥብቅ ሲፈለግ የነበረውን እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጫዋች ሰማያዊዮቹ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረማቸው ተገልጿል።
ተጫዋቹ ከቼልሲ ጋር የስድስት ዓመት ኮንትራት ተፈራርሟል።
የ23 ዓመቱ ሞርጀን ሮጀርስ ወደ ቼልሲ የሚያደርገውን ዝውውር ካጠናቀቀ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ለእኔ ቼልሲ የለንደን ትልቁ ክለብ ነው” ሲል ተናግሯል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሊ አህመድ አዲስ አበባ ገባ
በታሪካዊው ምስል የተገናኙት ሜሲ እና ያማል፤ በዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ፊት ለፊት!
አርሰናል ክርስቶስ ዞሊስን ለማስፈረም ተስማማ