የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጉራጌ ዞን አገና ከተማ ተጀመረ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር) የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጉራጌ ዞን አገና ከተማ አስጀምረዋል፡፡
በጉራጌ ዞን በአገና ከተማ የአንዲት አረጋዊት ቤት በማፍረስ አዲስ የግንባታ ስራ ዶ/ር መሀመድ አስጀምረዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ መሀመድ ኑርዬ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልል እና የጉራጌ ዞን አመራሮች የተገኙ ሲሆን በአገና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የአረንጓዴ አሻራ አሳርፈዋል።
“በጎነት እና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መርህ በተከናወነው በዚህ ተግባር የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች እና የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፡ ምትኬ ገ/ወልድ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል