ክረምትና የበቆሎ እሸት

ክረምትና የበቆሎ እሸት

በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች በክረምት ወቅት የበቆሎ እሸት ጥብስ እና ቅቅል በየመንገድ ዳሩ ሲሸጥ ማየት የተለመደ ነው፡፡

በሀዋሳ ከተማም በክረምት ወቅት በየመንገድ ዳር የበቆሎ ጥብስ እና ቅቅል ገበያው ይደራል፡፡

ክረምትና እሸት የማይነጣጠሉ እስኪመስሉ ድረስ በተለይም አመሻሽ አካባቢ ሰዎች ከስራ ገበታቸው ሲወጡ፣ የማታ የእግር ተጓዦች( ወክ የሚበሉ ) እና ሌሎችም በአጋጣሚ በመንገዳቸው ሲያልፉ ያጋጠማቸው ሰዎች በየመንገዱ ሽታው የሚያውደው የበቆሎ ጥብስና ቅቅል በመግዛት የክረምቱን ቅዝቃዜ ያስታግሳሉ፡፡

ከዛም አልፎ እሸት በመግዛት ወደ ቤቱ ይዞ የሚሄድ ሰው ቁጥርም ብዙ ነው፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ በየጎዳናው በቆሎን በመጥበስና በመቀቀል ለገበያ የሚያውሉ ሰዎች ኑሯቸውን ለመደጎም እንደ ገቢ ምንጭ አማራጭ ይጠቀሙታል፡፡

በሀዋሳ ጎዳናዎች በቆሎ ሲሸጡ ያገኘናቸው ነጋዴዎችም በተለይም በዚህ በክረምት ወቅት ገበያው እንደሚደራ ገልጸው በቆሎ በእሸት፣ በጥብስና በቅቅል መልኩ አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

አዘጋጅ ፡ ሰብለ ደምሴ