አሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለው ዳኛ የአውሮፓ ሱፐር ካፍ የፍፃሜ ጨዋታን እንዲመራ ተመረጠ

አሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለው ዳኛ የአውሮፓ ሱፐር ካፍ የፍፃሜ ጨዋታን እንዲመራ ተመረጠ

በዓለም ዋንጫው ላይ ጨዋታዎችን ለመመራት ወደ አሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለው ሶማሊያዊው የእግር ኳስ ዳኛ ኡመር አርታን የአውሮፓ የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን በዋና ዳኝነት እንዲመራ ተመርጧል።

ኡመር አርተር በኦስትሪያ ሳልዝቡርግ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ፒኤስጂ እና በኢሮፓ ሊጉ አሸናፊ አስቶንቪላ መካከል የሚካሄደውን የሱፐር ካፕ ጨዋታን እንዲመራ መመረጡን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል።

የ34 ዓመቱ ዳኛ የዓለም ዋንጫን እንዳይመራ መከልከሉ ዕጣ ፈንታ መሆኑን ገልፆ ነበር።

አርታን በትናንትናው ዕለት በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በደረሰበት ወቅት የጀግና አቀባበል ተደርጎለታል።

ፒኤስጂ ከአስቶንቪላ ጋር የሚያደርጉት የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ ረቡዕ ነሀሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም በሬድ ቡል አሬና ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ