የዲጂታል ዘመን ኮሙኒኬሽን የመረጃ ስርጭት ብቻ ሳይሆን የሕዝብ እምነት የሚገነባበት እና የተቋማትን ገጽታ የሚያጠናክር መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የዲጂታል ዘመን ኮሙኒኬሽን የመረጃ ስርጭት ብቻ ሳይሆን የሕዝብ እምነት የሚገነባበት እና የተቋማትን ገጽታ የሚያጠናክር ነው ሲሉ በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ገለፀ።
በዚህ ዘመን ኮሙኒኬሽን የመረጃ ስርጭት ብቻ ሳይሆን፤ የሕዝብ እምነት የሚገነባበት፣ የተቋማትን ገጽታ የሚያጠናክር፣ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የሚፈጥር ጭምር ነው ያሉት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒከሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢዘዲን ከድር ናቸው።
የመረጃ ስርጭት በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ስትራቴጂካዊ ዘርፍ ነውም ብለዋል።
በወረዳው በበጀት ዓመቱ በሚዲያ ግንኙነት፣ በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ በሕዝብ ግንኙነት፣ በመረጃ ስርጭት እና በተቋማዊ ገጽታ ግንባታ የተመዘገቡ ስኬቶች ውጤታማ እንደነበሩ የገለጹት ኃላፊው፥ የወረዳውን ፀጋዎች በማስተዋወቅና ገፅታን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት መደረጉን አስታውቀዋል።
ሀገራዊ ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን ትልቅ ድርሻ እንደነበረው አውስተው፥ ሀገራዊ ምክክሩን አስመልክቶም ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ ለማድረስ በየደረጃው በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
በተለይም በተያዘው በጀት አመት ዓላማ ተኮር ኮሚኒኬሸን በማስረጽ የመረጃ ጥራትን ለማሻሻል፣ መረጃን በወቅቱ በማድረስ፣ ዲጂታል ኮሚኒኬሽንን በማጠናከር፣ የሕዝብ ተሳትፎን በማሳደግ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለን ትብብር በማጠናከር ተቋም ለመገንባት እንደ መዋቅር የተዘጋጀ ዕቅድ ተግባራዊነቱ ሲለካ ለተቋሙም ሆነ ለወረዳው ሕዝብ ተጨባጭ ውጤት ያስመዘገበ ነበር ብለዋል።
በወረዳው ማህበራዊ ሚዲያን ለልማትና ለበጎ አላማ በመጠቀም ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ተግተው እየሰሩ መሆኑን ያነሱት አቶ ኢዘዲን፥ ማህበረሰቡ መረጃዎችን ከእውነተኛ ምንጮች ወስዶ የመጠቀም ልምድ እንዲያዳብር እና አሉታዊ ሃሳቦችን በጋራ መታገል ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: ሀጅራ ግርማ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ሀገራችን ኢትዮጵያ በእውቀት፣ በክህሎትና በስነ-ምግባር የበለፀገና የሰለጠነ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት በአዳዲስ ፈጠራና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል – ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ
ከ5ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በበይነ መረብና በወረቀት እያስፈተነ መሆኑን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ገለፀ
የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተሻሻለ የስልጠና ጥራት፣ በተጠናከረ የኢንዱስትሪ ትስስርና ተፈላጊ ሙያተኞችን በማፍራት በክልሉ ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ አስታወቀ