የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የቤት ልማት አቅርቦት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ለበርካታ ዘመናት ለነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የይርጋጨፌ ከተማ ከንቲባ አቶ ብዙአየሁ ታደሰ፤ ከተማውን ለመቀየር በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ካሉት መካከል አንዱ የቤቶች ልማት ግንባታ መሆኑን አንስተዋል፡
የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የቤቶች ልማት አቅርቦት ወሳኝ ነው ብለው፤ የተገነቡ ቤቶችም ደረጃቸውን የጠበቁ፣ ለኑሮ ምቹና የተሟላ የመሠረተ ልማት አገልግሎት ያለበትና ከቀድሞ የተሻሉ መሆኑን ከንቲባው አብራርተዋል።
የተገነቡ ቤቶች የከተማዋን የኢንቨስትመንት፣ የገቢ ዕድገትና አቅም ለማሳደግና ከተማዋን ለማልማት ያስችል ዘንድ ለልማት ተነሺ ለሆኑና ለበርካታ ጊዜ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለነበረባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ቤቶቹ የሚሠጡ መሆኑን ከንቲባው አብራርተዋል።
በመሆኑም ከኢፍትሃዊነት በፀዳ መልኩ የቤቶቹ ዕደላ በዕጣ የሚተላለፍ መሆኑን አቶ ብዙአየሁ አስረድተዋል።
የይርጋጨፌ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብርሃም ሆርዶፋ እንደገለፁት፤ ለማህበረሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠትና ከተማዋን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በትኩረት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
እንደሀገር ከተጀመሩ ኢንሼቲቮች መካከል አንዱ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት በመሆኑ እንደ ከተማ አርባ ቤቶችን በአርባ ቀን ገንብተው ማስተላለፍ መቻላቸውን አንስተዋል።
በመርሀ ግብሩ የተገኙ ታዛቢዎችም በተለይም ምርጫውን በሠላም በተሳካ ማግስት የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት በተደረጉ ተግባራት መደሰታቸውን አመላክተዋል።
ዘጋቢ: ፅጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ማሳቸውን ለመኸር እርሻ ደጋግማው በማረስ አለስልሰው በወቅቱ ለመዝራት መዘጋጀታቸውን በከምባታ ዞን ቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ያነጋገርናቸው አንዳንድ አርሶአደሮች ተናገሩ
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ከ40 ሺህ በላይ ወጣቶችን ተሳታፊ በማድረግ 46 ሚሊዮን 620 ሺህ ብር በላይ ከመንግሥት ሊወጣ የሚችለውን ለማዳን ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስታወቀ
የቀቤና ልዩ ወረዳ ማህበረሰብ የልማት ፍላጎት ማሟላት የሚቻለው ግብርና ታክስ በታማኝነትና በወቅቱ መክፈል ሲቻል መሆኑ ተገለጸ