የቡታጅራ ግራንድ ቪው ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን 164 ተማሪዎች ለ2ኛ ዙር አስመረቀ
የቡታጅራ ግራንድ ቪው ኮሌጅ ዲንና ባለቤት አቶ ሰለሞን ምፍታ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ትምህርት ዛሬ የሚዘራ ዘር፥ ነገ የሚታጨድ ፍሬ ነው” በማለት መማር የማያልቅ ጉዞ መሆኑን አመላክተዋል።
ምረቃ የትምህርት ፍጻሜ ሳይሆን የአዲስ እውቀት ጉዞ መጀመሪያ መሆኑን የጠቆሙት ዲኑ፤ ግራንድ ቪው ኮሌጅ ለ2ኛ ዙር 164 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች ማስመረቁን ገልፀዋል።
ተመራቂዎች በተመረቁበት የሙያ ዘርፍ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በትጋት፣ በታማኝነት እና በሙያዊ ሥነ-ምግባር እንዲያገለግሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ተወካይና የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ መስፍን ኮርማ፤ ተመራቂዎቹ በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ሀገራቸውን ለማገልገል ሊዘጋጁ እንደሚገባ ጠቁመው ሥራ ፈላጊዎች ብቻ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪዎች በመሆን ለራሳቸውና ለሌሎች የሥራ እድል በመፍጠር ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።
ሌላኛው በዕለቱ የተገኙት የአትላስ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ ዲንና ባለቤት ታጋይ ምፍታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትምህርቱ ዘርፍ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በመጠቆም ሀገሪቱ ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ ልህቀት ደረጃ ለመድረስ መማር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ለተመራቂ ተማሪዎችም የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተመራቂ ተማሪዎችም በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ማህበረሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ: ታምሬ አበበ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው