የአብሮነት ምልዕክት
ወ/ሮ ፋጡማ መቻል የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ስትሆን የእስልምና ዕምነት ተከታይ ናት።
በነገው ዕለት በሀዋሳ በድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በዓልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ሀዋሳ ከተማ የመጡ እንግዶችን ስትቀበል አግኝተን ያነጋገርናት ሲሆን በዓሉን በአብሮነት በሰላም እንዲከበር ከሌሎች የከተማ ነዋሪዎች ጋር በመሆን እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ብላ መቀበሏ ደስታ እንደፈጠረላት ትገልጻለች።
ሀዋሳ ከተማ ሁሉም ሀይማኖቶች በፍቅር፣ በመተሳሰብና በአንድነት የሚኖሩቧት ከተማ እንደሆነች ወ/ሮ ፋጡሟ የተናገረች ሲሆን ለመላው የክርስትና እምነቱ ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፋለች።
ዘጋቢ: ፋሲል ሀይሉ
የአብሮነት ምልዕክት

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው