የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጥናታቸው በተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ የማረጋገጫ ወርክሾፕ እና የርክክብ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ላይ የማረጋገጫ ወርክሾፕ እና የርክክብ መርሃ ግብር ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማካሄድ ጀምሯል።
ሀገር በቀል እውቀት ለዘመናዊ እውቀት መሠረት በመሆኑ ከዘመናዊ ጋር ተሳስሮ እንዲቀጥል በጥናትና ምርምር እንዲዳብር ማድረግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድርሻ ነው።
ስለሆነም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሀገር በቀል እውቀቶችን በማሰባሰብ በመሰነድና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ጥናትና ምርምር እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።
ፕሮጀክቶቹ የሚያተኩሩት ባህል፣ እውቀትና ቅርስ ጉራጌ ሀብ (Gurage Hub, Cross-Platform System for Gurage Cultures and Values”) የተሰኘው ቴክኖሎጂ እና የጉራጌ ማህበረሰብ መገለጫ የሆነውን ጀፎረ ላይ እንደሆነ ተመላክቷል።
በመድረኩ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱልሙህሲን ሀሰን፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለ፣ የሁለቱ ጉራጌ ዞን አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ሄኖክ ተክሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት የቤት ልማት አቅርቦት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
35 በመቶ የሚሆኑ ውሃ አዘል መሬቶች እየጠፉ መምጣታቸውን የተለያዩ ጥናቶች አመላካቱ
በሀገሪቱ የሚገኙ ውሃ አዘል መሬቶችንና ተፋሰሶችን የማልማት ተግባር በጥናት በማስደገፍ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ