35 በመቶ የሚሆኑ ውሃ አዘል መሬቶች እየጠፉ መምጣታቸውን የተለያዩ ጥናቶች አመላካቱ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደረገው ጥናትና ምርምር 35 በመቶ የሚሆኑ ውሃ አዘል መሬቶች እየጠፉ መምጣታቸውን የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመላከቱ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ገለጸ፡፡
በናቡ ኢትዮጵያና በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አማካይነት በውሃ አዘል መሬቶች ዙሪያ የተደረገውን ዳሰሳ ጥናት ተከትሎ በቦንጋ ከተማ ሲካሄድ የነበረው ምክክር መድረክ ተጠናቋል፡፡
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮ ሀብት ትምህርት ክፍል መምህር እና የዳሰሳ ጥናቱ ቡድን መሪ ዶክተር አብይ ጌታቸው ውሃ አዘል መሬቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተመናመኑ መምጣታቸው በናቡ ኢትዮጵያ አስተባባሪነት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ 35 በመቶ የሚሆኑ ውሃ አዘል መሬቶች መጥፋታቸው በጥናት መረጋገጡን ገልጸው፥ የውሃ አካላትን መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባ አሰገንዝበዋል፡፡
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ግርማ ጥላሁን የቀረበው የዳሰሳ ጥናቱ ለሌሎች ምርምር ስራዎች ትልቅ ዕገዛ እንዳለው አንስተዋል፡፡
መድረኩ አስተዳደራዊ ዕቅድ ለማዘጋጀት መነሻ ሀሳብ የተገኘበት ስለመሆኑም ተመላክቷል፡፡
ከተሳታፊዎች መካከል የቤንች ሸኮ እና የካፋ ዞን ግብርና፣ ደን አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል፣ አቶ አክሊሉ አማዴና ሌሎችም እንደገለጹት ናቡ ኢትዮጵያ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመቀናጀት የሰራቸው ሥራዎችና የዳሰሳ ጥናቱ ያስገኘውን ተሞክሮ አጠናክሮ ማስቀጠልና ተግባራዊ ማድረግ ይገባል በማለት አስተያየታቸው ሰጥተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ብዙአየሁ ጫካ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
ምክር ቤቱ በ2018 በጀት አመት ሪፖርት እና የ2019 ጠቋሚ እቅድ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ
በበጀት አመቱ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በበጀት ዓመቱ ከ379 ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)