ላሚን ያማል የዚህ ዓመት የላ ሊጋ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ
የስፔን ላ ሊጋ የ2025/2026 የውድድር ዘመን የላቀ ብቃት ላሳዩ ተጫዋቾች ሽልማቱን የሰጠ ሲሆን፣ የባርሴሎናው ታዳጊ ኮከብ ላሚን ያማል የውድድር ዘመኑ ምርጥ ተጫዋች በመሆን አሸናፊ ሆኗል።
የ18 ዓመቱ ተጫዋች ክሊያን ምባፔን እና ሞሪቂን በመብለጥ ነው ተሸላሚ የሆነው።
ላሚን ያማል በዘንድሮው የውድድር ዘመን በላ ሊጋው ባደረጋቸው 28 ጨዋታዎች ሙሉ በሙሉ በሜዳ ላይ የበላይነትን የያዘ አፈጻጸም አሳይቷል።
ለቡድኑ ባደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦም 28 የጎል ተሳትፎዎችን በማስመዝገብ፣ በእያንዳንዱ ጨዋታ አማካይ አንድ ግብ ወይም አሲስት በማስመዝገብ አስደናቂ ብቃቱን አረጋግጧል።
ያማል በዚህ የውድድር ዘመን 16 ጎሎችን ከማስቆጠሩ ባሻገር 12 ግብ የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ይህ ሽልማት ለላሚን ያማል የሙያ ህይወት ትልቅ ምዕራፍ ነው።
ተጫዋቹ በቀጣይ ዓመታት በአውሮፓ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች ምን ያህል የላቀ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ የእግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት እየጠበቁት ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
ላሚን ያማል የዚህ ዓመት የላ ሊጋ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

More Stories
በቀቤና ልዩ ወረዳ የቴኳንዶ ስፖርት ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በመሰራቱ ስፖርት ባህል እየሆነ መምጣቱን የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ አሚን በደዊ ገለጹ።
ማንቸስተር ዩናይትድ ኤደርሰንን ለማስፈረም ተስማማ
ካይ ሀቨርትዝ 3ኛው ተጫዋች ሆነ