ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ማይክል ኦሊሴ ላይ ዓይናቸውን ጣሉ!
በእግርኳስ ዓለም የዝውውር ገበያ ውስጥ ተጠባቂው የሪል ማድሪድ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሲቃረብ፣ የቡድኑ ፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ አድናቂዎችን የሚያስደስት ዜና ይዘው ቀርበዋል።
ምንም እንኳን በይፋ ቢክዱትም፣ የባየር ሙኒኩ ኮከብ ማይክል ኦሊሴ የሪል ማድሪድ ቀጣይ ዕቅድ ሆኗል።
ፔሬዝ በቅርቡ ለስፔን መገናኛ ብዙሃኖች በሰጡት መግለጫ፣ በመጪው ማክሰኞ ለአንድ ትልቅ ክለብ በታሪክ ከፍተኛ የሚባል 150 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።
ብዙዎች ስሙን ቢጠይቋቸውም፣ በስም ዝርዝራቸው ውስጥ የሌሉትን ተጫዋቾች በመጥቀስ ማይክል ኦሊሴን ጨምሮ ሃሪ ኬን እና ኤርሊንግ ሃላንድን “የእኔ ዕቅድ አካል አይደሉም” በማለት በይፋ አስተባብለዋል።
ሆኖም፣ ከተዓማኒ ምንጮች እየወጡ ያሉት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ፔሬዝ በድብቅ እያቀዱ ያሉት የዝውውር ጥያቄ ለፈረንሳዊው የባየር ሙኒክ ኮከብ ሚሼል ኦሊሴ ነው።
ነገር ግን የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ አቋም እጅግ ጠንካራ ሆኖ ተገኝቷል።የክለቡ የክብር ፕሬዚዳንት ኡሊ ሆነስ እንደተናገሩት”ኦሊሴን አንሸጥም! የ200 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ እንኳን ቢቀርብልን ለደጋፊዎቻችን ብለን አንሸጠውም”ብለዋል።
ሀላፊው አክለውም “በባንክ አካውንታችን ተጨማሪ 200 ሚሊዮን ዩሮ ይዘን በየሳምንቱ ደካማ እግርኳስ ከመጫወት፣ ኮከባችንን ይዘን በሜዳ ላይ መደሰትን እንመርጣለን” ሲሉ ተናግረዋል።
የ2025/26 ውድድር ዘመን የቡንደስሊጋው ምርጥ ተጫዋች የሆነው ኦሊሴ፣ ከባየር ሙኒክ ጋር እስከ 2029 ድረስ ውል አለው።
ምንም እንኳን የሪል ማድሪድ ፍላጎት እጅግ ግዙፍ ቢሆንም፣ የባየር ሙኒክ አስተዳደር ተጫዋቹ የረጅም ጊዜ ዕቅዳቸው ዋነኛ ምሰሶ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ምንም ዓይነት የሽያጭ ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።
ይህ የዝውውር ጉዳይ የፔሬዝን የወደፊት የፕሬዚዳንትነት ጉዞ እና የባየር ሙኒክን የጥንካሬ ፈተና የሚለካበት ይሆናል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ
ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ማይክል ኦሊሴ ላይ ዓይናቸውን ጣሉ!

More Stories
ላሚን ያማል የዚህ ዓመት የላ ሊጋ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ
በቀቤና ልዩ ወረዳ የቴኳንዶ ስፖርት ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በመሰራቱ ስፖርት ባህል እየሆነ መምጣቱን የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ አሚን በደዊ ገለጹ።
ማንቸስተር ዩናይትድ ኤደርሰንን ለማስፈረም ተስማማ