በቀቤና ልዩ ወረዳ የቴኳንዶ ስፖርት ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በመሰራቱ ስፖርት ባህል እየሆነ መምጣቱን የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ አሚን በደዊ ገለጹ።

በቀቤና ልዩ ወረዳ የቴኳንዶ ስፖርት ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ በመሰራቱ ስፖርት ባህል እየሆነ መምጣቱን የልዩ ወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ አሚን በደዊ ገለጹ።

ዋና አስተዳዳሪዉ ይህን የገለጹት ኡንጀሞ ወርልድ ቴኳንዶ ማዕከል ለ12ኛ ዙር ተማሪዎቹን በወልቂጤ ከተማ ባስመረቀበት ወቅት ነዉ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ አሚን በደዊ በዚህ ወቅት ስፖርት ለማህበረሰቡ ጤና፣ ልማትና ኢኮኖሚን ለማሳደግ ያለዉ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀቤና ልዩ ወረዳ የኡንጀሞ ወርልድ ቴኳንዶ ማሰልጠኛ ማዕከል ወጣቶች በስነምግባር ታንጸዉ እንዲያድጉ ከማድረግ ባሻገር ልዩ ወረዳዉን በመወከል በክልልና በሀገር ደረጃ አሸናፊ በመሆን ሜዳሊያዎችን ማምጣቱን አንስተዋል።

ማዕከሉ ተተኪ ስፖርተኞችን እና አሰልጣኞችን በማፍራት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝና ይህም የልዩ ወረዳዉ አስተዳደር በልዩ ወረዳው ባህል እየሆነ የመጣዉን የቴኳንዶ ስፖርት ዘርፍ ለማሳደግ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የኡንጀሞ ወርልድ ቴኳንዶ ማሰልጠኛ ማዕከል አሰልጣኝ ማስተር ሀዲሙ አክመል በበኩላቸዉ ማዕከሉ ወጣቶች በስነምግባር ታንፀዉ እንዲያድጉ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ማዕከሉ ባለፉት አመታት በርካታ ተማሪዎችን በቴኳንዶ ስፖርት በማስልጠን ላይ እንደሚገኝና በዚህም የተሻለ ዉጤት ተገኝቷል ነዉ ያሉት።

ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ተማሪዎችን በማስልጠን ላይ የሚገኘዉ ማዕከሉ ለ12ኛ ዙር በደማቅ ሁኔታ ማስመረቅ መቻሉን አሰልጣኙ ተናግረዋል።

ተማራቂ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየትም ስፖርት መስራታቸዉ ጤናቸዉን ከመጠበቀ ባለፈ በስነ ምግባር እንዲታነጹ እንዳስቻላቸዉ ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት በተለያዩ ክልላዊና ሀገር አቀፍ ዉድድሮች ላይ ተሳትፈዉ አሸናፊ እንደነበሩ በማስታወስ ወደፊትም ሀገራቸዉን ወክለዉ ለመወዳደር እንደሚሰሩ አስረድተዋል።

በምረቃ መርሃ ግብር ላይ የማስተር ሀዲሙ አክመል በቴኳንዶ ስፖርት ላይ ያተኮረ “የዝምታ እሳት” የተሰኘ የአማርኛ ፊልም ተመርቆ ለእይታ በቅቷል።

ዘጋቢ፡ ሪያድ ሙህዲን