ማንቸስተር ዩናይትድ ኤደርሰንን ለማስፈረም ተስማማ

ማንቸስተር ዩናይትድ ኤደርሰንን ለማስፈረም ተስማማ

ማንቸስተር ዩናይትድ የአታላንታውን አማካይ ኤደርሰንን ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል።

ዩናይትድ ለብራዚላዊው ተጫዋች ዝውውር 34 ሚሊዮን ፓውንድ የመጀመሪያ ክፍያ እና የተጫዋቾቹ ስኬት እየታየ የሚከፈል ተጨማሪ 3.8 ሚሊዮን ፓውንድ ለቤርጋሞው ክለብ ይከፍላል።

ኤደርሰን በቀያዮቹ ቤት እ.ኤ.አ እስከ 2030 ድረስ የሚያቆየውን ኮንትራት ለመፈራረም የተስማማ ሲሆን፣ በኮንትራቱ ተጨማሪ 12 ወራትን የማራዘም አማራጭ ተካቷል።

ስምምነቱ በኤደርሰን የጤና ምርመራ መጠናቀቅ ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ዝውውሩ ከሐምሌ ወር አስቀድሞ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ኤደርሰን በማይክል ካሪክ የቋሚ አሰልጣኝነት ዘመን የመጀመሪያው ፈራሚ በመሆን በቲያትር ኦፍ ድሪምስ የሚከሰት ይሆናል።

ዩናይትድ ለረጅም ጊዜ ሲከታተል የነበረውን ተጫዋች ለማስፈረም ቢቃረብም ካሴሚሮ ክለቡን በመልቀቁ እና ማኑኤል ኡጋርቴም ክለቡን የመልቀቅ ዕድሉ ከፍተኛ በመሆኑ፣በክረምቱ የዝውውር መስኮት ተጨማሪ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች እንደሚያስፈርም ይጠበቃል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ