ካይ ሀቨርትዝ 3ኛው ተጫዋች ሆነ
ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ካይ ሀቨርትዝ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ለሁለት የተለያዩ ክለቦች ጎል ያስቆጠረ 3ኛው ተጫዋች ሆኗል።
ካይ ሀቨርትዝ በሀንጋሪ ቡዳፔስት ከተማ በፑሽካሽ አሬና ስታዲየም እየታከሄደ በሚገኘው የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ፒኤስጂ ላይ ጎል አስቆጥሮ አርሰናል መሪ ማድረግ ችሏል።
ይህንን ተከትሎ ካይ ሀቨርትዝ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ(ማንቸስተር ዩናይትድ፣ሪያል ማድሪድ) እና ከማሪዮ ማንዙኪች(ባየርን ሙኒክ፣ዩቨንቱስ) በመቀጠል በሻምፒዮንስ ሊጉ ፍፃሜ ጨዋታ ጎል ያስቆጠረ 3ኛው ተጫዋች ሆኗል።
ካይ ሀቨርትዝ ከዚህ ቀደም የቼልሲ ተጫዋች በነበረበት ወቅት ማንቸስተር ሲቲ ላይ ጎል አስቆጥሮ ሰማያዊዮቹን የሻምፒዮንስ ሊግ ባለድል ማድረጉ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።