አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ከ44 ቀናት ቆይታ በኋላ ቶትንሃምን ለቀቁ
ቶትንሃም ከአሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር በስምምነት መለያየቱን አሳውቋል።
ክሮሺያዊው አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ከአምስት ሳምንታት በፊት ተሰናባቹን አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክን ተክተው እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ክለቡን መረከባቸው ይታወሳል።
በጊዚያዊ አሰልጣኝነት ክለቡን የተረከቡት የ47 ዓመቱ አሰልጣኝ በሰሜን ለንደኑ ክለቡ የቆይታ ጊዚያቸው ከ44 ቀናት ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።
ያስመዘገቡት ደካማ ውጤት ከስፐርሶች ጋር ለመለያየታቸው ዋነኛው ምክንያት ነው።
ክለቡን በፕሪሚዬር ሊጉ ከመውረድ ስጋት እንዲታደጉ የተሾሙት ቱዶር ካከናወኗቸው 5 ጨዋታዎች አንድም ጊዜ ሳያሸንፉ ተሰናብተዋል።
አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር በቶትንሃም በሁሉም ውድድሮች ካከናወኗቸው 7 ጨዋታዎች ውስጥ ማሸነፍ የቻሉት አንዱን ብቻ ነው።
ቶትንሃም በፕሪሚዬር ሊጉ ከወራጅ ቀጠናው በአንድ ነጥብ ብቻ ርቆ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡- ሙሉቀን ባሳ

More Stories
የአንደኛ ደረጃ አትሌትክስ አሰልጣኞች ተመረቁ
ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን የክለቡ ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ለማስፈረም ተስማማ
ሶስቱ ብቸኛ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች