የአንደኛ ደረጃ አትሌትክስ አሰልጣኞች ተመረቁ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የጎፋ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ በጋራ በመሆን የአንደኛ ደረጃ አትሌትክስ አሰልጣኞች አሰልጥኖ አስመርቋል።
በስልጠናው ከአምስት ዞኖች የተወጣጡ 23 አሰልጣኞች ለ15 ቀናት የተሰጠውን ስልጠና አጠናቀው መመረቃቸው ተገልጿል።
የጎፋ ዞን ባህልና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ንክሰን ለማ በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ እንደገለጹት ስልጠናውን ተከታትለው ያጠናቀቁ አሰልጣኞች ወደ መዋቅራቸው ሲመለሱ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ክልሉንና ሃገርን የሚያስጠሩ ውጤታማ አትሌቶችን ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የአትሌቲክስ ስፖርቱን በእውቀትና በአሰራር ማዕቀፍ ለማዘመን የአሰልጣኞች ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የጎፋ ዞን በርካታ አትሌቶች የሚፈልቁበት የአትሌትክስ አቅም ያለው ዞን መሆኑን ጠቅሰው፥ ይህንን ጸጋ በአግባቡ በመጠቀም ለዘርፉ ዕድገት በትኩረት እንደሚሰራ አንስተዋል።
ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ስፖርታዊ ውድድሮችን የማስፋትና ዘርፉን በእውቀት የመምራት ጥረቶች
ተጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሏል።
ተመራቂዎች በሰጡት አስተያዬት ወደፊት በክልልና በአገር ደረጃ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የአሰልጣኞች ስልጠና ወሳኝ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን የክለቡ ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ለማስፈረም ተስማማ
ሶስቱ ብቸኛ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች
ቼልሲ ማርኮ ፓሌስትራን ለማስፈረም ተስማማ