የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የግብርና ስራዎችን ተመለከተ
በቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ልክነሽ ስርገማ የተመራው የቅኝት ቡድን በቁሊቶ ከተማ በተለያዩ ተቋማት እየለሙ ያሉ የግብርና ስራዎችን ተመልክቷል።
በቁሊቶ ከተማ ዕድገት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የቁሊቶ ማረሚያ ተቋም፣ የስላሴና ማርያም ቤተክርስቲያኞች ውስጥ እየለሙ ያሉ የግብርና ስራዎች ምልከታ ተደርጎባቸዋል።
በተቋማቱ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የቡና ምርት በወጉ እየተሰራበት መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ተመልክቷል።
በከተማው የሚገኙ ሁሉም ተቋማት የግብርና ስራዎችን እያለሙ ሲሆን በምግብ ራስን ለመቻል የተጀመረውን ውጥን ዳር ለማድረስ አጋዥ ናቸው ተብሏል።
ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ