የኣሪ ዞን የ2018 ዓ.ም ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር ተጀመረ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 20/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን የ2018 ዓ.ም ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በጂንካ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
3ኛው ዞናዊ ልዩ ልዩ የስፖርት ሻፒዮና በ7 የውድድር አይነቶች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት በሁለቱም ፆታ እንደሚካሄድ ተመላክቷል።
በዞኑ የስፖርት ምክር ቤት አዘጋጅነት በተሰናዳው ውድድር ተገኝተው መልክት ያስተላለፉት የስፖርት ምክር ቤቱ ሰቢሳቢና የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ፥ ስፖርት ወንድማማችነትና ሠላምን ለመገንባት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀው፥ ውድድሩ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል።
ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትና የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማጠናከር ውድድሩ የጎላ ጠቄሜታ እንዳለው የገለፁት የኣሪ ዞን ባህልና ስፖርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጋልሺ፥ ዞናዊ ውድድሩ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ7 የስፖርት አይነቶች ሁሉም መዋቅሮችና ጂንካ ዩንቨርሲቲን ጨምሮ በሁለቱም ፆታ እንደሚሳተፉ አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶር ከ39 ቀናት ቆይታ በኋላ ቶትንሃምን ለቀቁ
ዲሚትሪ ፓዬት ጫማውን ሰቀለ
ቤን ዋይት ከዓመታት በኋላ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀረበለት