ዲሚትሪ ፓዬት ጫማውን ሰቀለ
ፈረንሳዊው የመሀል ስፍራ ተጫዋች ዲሚትሪ ፓዬት ራሱን ከእግርኳስ ተጫዋችነት ማግለሉን አሳውቋል።
የቀድሞ የዌስትሃም ዩናይትድ እና ኦሎምፒክ ማርሴ ተጫዋች ፓዬት በ38 ዓመቱ ነው ጫማ መስቀሉን ያሳወቀው።
ዲሚትሪ ከሁለቱ ክለቦች በተጨማሪ ለናንትስ፣ሴንት ኢቴይን፣ሊን እና ለብራዚሉ ቫስኮ ዳካማ ተጫውቶ አሳልፏል።
20 ዓመታትን በእግርኳሱ ዓለም በትልቅ ደረጃ የተጫወተው ፓዬት ለፈረንሣይ ብሔራዊ ቡድን በ38 ጨዋታዎች ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ካርሎስ ባሌባ ለማንቼስተር ዩናይትድ ፊርማውን አኖረ
አርሰናል ከ ላምፓርዱ ኮቨንተሪ ሲቲ
አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈረመ