በክልሉ በ5ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከ6 መቶ ሺ በላይ ህፃናት ተጠቃሚ ይሆናሉ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 18/2018 (ደሬቴድ) ከ631 ሺህ በላይ ህፃናት ተደራሽ እንደሚሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ገልጿል።
ክልላዊ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መረሐ-ግብር በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።
ክትባቱ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከመጋቢት 18-21/2018 ዓ.ም ድረስ ቤት ለቤት ይሰጣል።
በዘመቻው በመደበኛው የክትባት መርሀ-ግብር ተደራሽ ያልሆኑና ክትባት ጀምረው የቋረጡ ህፃናት የክትባቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ተመላክቷል።
የፌስቱላ ችግር የገጠማቸው እናቶች ፣ በተፈጥሮ ቆልማማ እግር ያላቸው ህፃናት፣ የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸውንም የመለየት ሥራ ከዘመቻው ጎን ለጎን ይከናወናል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በክልል ደረጃ በፖሊዮ ክትባት ዘመቻው ከ631 ሺህ በላይ ህፃናት ተደራሽ ይደረጋሉ ብለዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ የክትባት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ያስታወሱት ኃላፊው ወላጆች ተገቢውን ትብብር በማድረግ እንዲያስከትቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወሰን ጨመሳ በበኩላቸው ዘመቻውን ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ፍቅሩ በላይ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ 5ኛው ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻው በክልሉ ከ 1.1ሚሊየን በላይ ህፃናት የክትባት መርሐግብሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ
በኮንታ ዞን አመያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የእናቶች እና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ
የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በይፋ መጀመሩን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ