በክልሉ 5ኛው ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻው በክልሉ ከ 1.1ሚሊየን በላይ ህፃናት የክትባት መርሐግብሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ
ከመጋቢት 18-21 2018 ቤት ለቤት የሚሰጠውን 5ኛ ዙር የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አስመልክቶ የሲዳማ ክልል የማስጀመሪያ ፕሮግራም በወንዶገነት ወረዳ ቦርጃ ቀበሌ በአሩማ ጤና ጣቢያ ተካሂዷል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሠላማዊት መንገሻ በማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ በተሠራው ጠንካራ የቅድመ መከላከል ሥራ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመዋል።
5ኛው የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸው በተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻው በክልሉ ከ 1.1ሚሊየን በላይ ህፃናት የክትባት መርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለው የፖሊዮ ክትባት ሲሰጥ ጎን ለጎን የከንፈር መሰንጠቅ ፣ የላንቃ መቀደድ ፣የፌስቱላ እና ሌሎች በሽታዎች ለማከም የሚያስችል ቅድመ ልየታ ይደረጋል ብለዋል።
የክትባት ዘመቻው ከመጋቢት 18 እስከ 22 2018 ዓም ድረስ የሚደረግ ሲሆን በሲዳማ ክልል ደረጃ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆናቸው ከ1.1 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህፃናት ይከተባሉ ተብሎ ይጠባቃል።
ዘጋቢ: ግዛቸው ደሳለኝ

More Stories
የወባ ቅድመ መከላከል ስራ ውጤት እያስገኘ መምጣቱን በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ
በኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የደቡብ ማዕከል ድጋፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ ሩዝ ያመረቱ አርሶ አደሮች ምርታማ መሆናቸውን ገለፁ
በክልሉ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ እናቶችና ሴቶች ተደራሽ በማድረግ ጤናቸው እንዲጠበቅ በትኩረት መሠራቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ