ሞሮኮ እና ብራዚል ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ ጀርመን ተሰናበተች
በ2026 የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሞሮኮ እና ብራዚል ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወደ 16ቱ ውስጥ ሲያልፉ ጀርመን ከውድድሩ ተሰናብታለች።
በዓለም ዋንጫ መድረክ ግማሽ ፍፃሜ በመድረስ ከአፍሪካ ፈርቀዳጅ የሆነችው ሞሮኮ ኔዘርላንድን በመለያ ምት 3ለ2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሻግራለች።
የአትላስ አንበሳዎቹ በቀጣዩ ዙር ከሦስቱ አስተናጋጅ ሀገራት መካከል አንዷ ከሆነችው ካናዳ ጋር ይጫወታሉ።
በሌላ ጨዋታ አምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫን በማንሳት ቀዳሚ የሆነችው ብራዚል ጃፓንን ከመመራት ተነስታ 2ለ1 በማሸነፍ የሚቀጥለውን ዙር ተቀላቅላለች።
ለሴሌሳዎቹ ወሳኝ የማሸነፊያ ጎሎችን ካሴሚሮ እና ጋብርኤል ማርቲኔሊ አስገኝተዋል።
በአሰልጣኝ ጁሊያን ናግልስማን የምትመራው ጀርመን በአንፃሩ በፓራጓይ በመለያ ምት 4ለ3 ተሸንፋ ከውድድሩ ተሰናብታለች።
ፓራጓይ በቀጣይ የፈረንሳይ እና የስዊድን አሸናፊን የምትገጥም ይሆናል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
ሞሮኮ እና ብራዚል ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ ጀርመን ተሰናበተች

More Stories
የአንደኛ ደረጃ አትሌትክስ አሰልጣኞች ተመረቁ
ማንቸስተር ሲቲ ኤሊዮት አንደርሰንን የክለቡ ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ለማስፈረም ተስማማ
ሶስቱ ብቸኛ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች